Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

protectdc

Protect DC
Menu

የግል ዘርፍ አጋሮች

Private Sector partnersንግድ ተቋማት እና ድርጅቶች የስራ-ቦታ እና የሰራተኞቻቸው ደህንነትን በማረጋገጥ ውስጥ ወሳኝ አጋሮች ናቸው። Protect DC በስራ ቦታ አሳሳቢ ባህሪያትን ወይም ንግግርን ለመለየት ከግል ዘርፍ ጋር ቅንጅት ይፈጥራል እና የጥቃት መከሰት እድልን ለመቀነስ ግብዓቶችን በማቅረብ ውስጥ ያግዛል።

Step 1የደህንነት ባህልን ማሳደግ 

የግል የንግድ ተቋማት ሰራተኞቻቸው ስለ አሳሳቢው ባህሪይ ወይም ንግግር ለተገቢ ባለ-ስልጣናት እንዲያሳውቁ በማበረታታት የደህንነት ባህልን ማሳደግ ይችላሉ። አስተዳዳሪዎች፣ ሰራተኞች፣ እና ደንበኞቻቸው ስጋቶቻቸውን እንዲያጋሩ ማበረታታት የህግ አስከባሪ ባለ-ስልጣናት ጣልቃ እንዲገቡ እና የጥቃት ሁኔታዎችን ለመቀነስ አስፈላጊ ግብዓቶችን እንዲያቀርቡ ያስችላል። ሪፌራልን እዚህ ያስቀምጡ።

Step 2የስልጠና እድሎች ውስጥ መሳተፍ

የማህበረሰብ አባላት አሳሳቢ ባህሪይ ወይም ንግግርን ለመለየት የመጀመሪያ የመከላከያ መስመር ናቸው። አንድ ማህበረሰብ ምን እንደሚፈልግ እና እንዴት ሪፌራል ማስገባት እንዳለበት ሲገነዘብ፣ የProtect DC ቡድን በተሻለ ሁኔታ የግለሰብ ህዝባዊ ደህንነት ፍላጎቶችን መደገፍ እና የጥቃት እቅዶችን ማቋረጥ ይችላል። የባሕርይ አደጋ ግምገማና አስተዳደር መሠረታዊ ኮርስ የማኅበረሰቡን አጋሮችና ድርጅቶች የመከላከያ ጥረቶችን ለማሻሻል ከጥቃት ጋር ተያይዘው የሚመጡ ጠቋሚዎችን ያሠለጥናል ። ለተጨማሪ መረጃ፣ Protect DC ያነጋግሩ።

Step 3የ DC HSEMA የንግድ ስራ የድንገተኛ ሁኔታ መቆጣጠሪያ አሰራሮች ማእከል ይቀላቀሉ 

የንግድ ስራ የድንገተኛ ሁኔታ መቆጣጠሪያ አሰራሮች ማእከል (ቢዝነስ ኢሜርጀንሲ ማኔጅመንት ኦፔሬሽንስ ሴንተር) (BEMOC) የክስተት ጊዜ የድንገተኛ ሁኔታ መረጃን በማጋራት፣ ስልጠናዎችን በማቅረብ፣ እና ለረጅም ጊዜ ማገገሚያ ቁልፍ መረጃ በማቅረብ የዲሲ የግል አጋሮችን ይረዳል። BEMOC ከድንገተኛ ሁኔታ በፊት፣ ወቅት፣ እና በኋላ የሁኔታ ንቃትን በመጠበቅ ውስጥ የንግድ ተቋማትን ያግዛል።

Partner Resources: