Sorry, you need to enable JavaScript to visit this website.

protectdc

Protect DC
Menu

ወላጆ ች፣ ተንከባካቢዎች እና ቤተሰቦች

Parents with Childrenደህንነት ያላቸው ማህበረሰቦች ጤናማ፣ ትጉ ቤተሰቦች እንዲወጡ ያስችላሉ። Protect DC የቤተሰቦቻቸው ጤና እና ደህንነትን ለመጠበቅ እንዲሆን፣ የጥቃት ወይም ከባድ ጉዳት አደጋን ለመገምገም እና ለተከታዮቻቸው እና ተቋሞቻቸው የጣልቃ-መግባት እርምጃዎችን ለማዘጋጀት፣ ከወላጆች እና ተንከባካቢዎች ጋር ይሰራል።

ከታች የተዘረዘሩት ወላጆች እና ተንከባካቢዎች ቤተሰቦቻቸውን መጠበቅ የሚችሉባቸው ሶስት መንገዶች ናቸው።

Step 1የደህንነት ባህልን ማሳደግ

እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል በቤታቸው ውስጥ ጥቃትን ለመከላከል ሚና አላቸው። የቤተሰብ አባላት አንድ ሰው አሳሳቢ ባህሪይ ወይም ንግግር ሲያሳይ ለ Protect DC ቡድን በማሳወቅ፣ ተገቢ የመንግስት ባለ-ስልጣናት ጣልቃ እንዲገቡ በማስቻል እና የጥቃት ሁኔታዎች የመከሰት እድልን ለመቀነስ አስፈላጊ መገልገያዎችን በማቅረብ ቤተሰቦቻቸውን መጠበቅ ይችላሉ። ሪፌራልን እዚህ ያስቀምጡ።

Step 2የስልጠና እድሎች ውስጥ መሳተፍ

የማህበረሰብ አባላት አሳሳቢ ባህሪይ ወይም ንግግርን ለመለየት የመጀመሪያ የመከላከያ መስመር ናቸው። አንድ ማህበረሰብ ምን እንደሚፈልግ እና እንዴት ሪፌራል ማስገባት እንዳለበት ሲገነዘብ፣ የProtect DC ቡድን በተሻለ ሁኔታ የህዝብ ደህንነት ፍላጎቶችን መደገፍ እና የጥቃት እቅዶችን ማቋረጥ ይችላል። የባሕርይ አደጋ ግምገማና አስተዳደር መሠረታዊ ኮርስ የማኅበረሰቡን አጋሮችና ድርጅቶች የመከላከያ ጥረቶችን ለማሻሻል ከጥቃት ጋር ተያይዘው የሚመጡ ጠቋሚዎችን ያሠለጥናል ። ለተጨማሪ መረጃ፣ Protect DC ያነጋግሩ።

Step 3እባክዎ 211 Answers, Please! ጋር ይደውሉ

የ 211 Answers, Please! ፕሮግራም መሰረታዊ የሰው ፍላጎቶችን እንደ ምግብ፣ መጠለያ የገንዘብ እርዳታ እና ጤና እንክብካቤን ለዲስትሪክቱ ነዋሪዎች እገዛ ይሰጣል። እነዚህ አገልግሎቶች የሚጨምሩት፣ ግን በእነዚህ ብቻ ያልተወሰኑት፣ ሚስጥራዊ የስልክ ድጋፍ፣ የቀውስ ጣልቃ-ገብነት፣ የሪፌራል እርዳታ፣ እና ለጤና እና የሰብዓዊ የማህበራዊ አገልግሎት ድጋፍ የቀጥታ ትስስር። ይህ አገልግሎት በቀን 24-ሰዓታት፣ በሳምንት ሰባት ቀናት፣ ወደ 211 Answers, Please! የጥሪ ማእከል ላይ በ 211 ወይም (202) 463-6211 ወይም or using the portal. (ፖርታል በመጠቀም ይገኛል።)

የአጋር የተጠቃሚ ቁሳቁሶች፥