ደህንነት ያላቸው እና ድጋፍ ሰጪ የመማሪያ አካባቢዎች ተማሪዎች በሙሉ አቅማቸው እንዲሰሩ ያስችላሉ። Protect DC የጥቃት ወይም ከባድ ጉዳት አደጋን ለመገምገም እና ለተከታዮቻቸው እና በማህበረሰባቸው ውስጥ አሳሳቢ ለሆኑ ግለሰቦች የጣልቃ-መግባት እርምጃዎችን ለማዘጋጀት ከትምህርት ቤት ማህበረሰቦች ጋር ይሰራል።
ከታች የተዘረዘሩት ማህበረሰቦች የትምህርት ቤታቸውን ጤና እና ደህንነት መጠበቅ የሚጀምሩባቸው መንገዶች ሶስት መንገዶች ናቸው።
ደረጃ 1፥ የደህንነት ባህልን ማሳደግ
ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቻቸው እና ሰራተኞቻቸው ስለ አሳሳቢው ባህሪይ ወይም ንግግር ለተገቢ ባለ-ስልጣናት እንዲያሳውቁ በማበረታታት የደህንነት ባህልን ማሳደግ ይችላሉ። ተማሪዎች፣ አስተማሪዎች፣ እና ሰራተኞች ስጋቶቻቸውን እንዲያጋሩ ማበረታታት የህግ አስከባሪ ባለ-ስልጣናት ጣልቃ እንዲገቡ እና የጥቃት ሁኔታዎችን ለመቀነስ አስፈላጊ ግብዓቶችን እንዲያቀርቡ ያስችላል። ማንነትዎን የማይገለጽበት ሪፌራል ይስጡ።
ደረጃ 2፥ የስልጠና እድሎች ውስጥ መሳተፍ
የማህበረሰብ አባላት አሳሳቢ ባህሪይ ወይም ንግግርን ለመለየት የመጀመሪያ የመከላከያ መስመር ናቸው። አንድ ማህበረሰብ ምን እንደሚፈልግ እና እንዴት ሪፌራል ማስገባት እንዳለበት ሲገነዘብ፣ የProtect DC ቡድን በተሻለ ሁኔታ የህዝብ ደህንነት ፍላጎቶችን መደገፍ እና የጥቃት እቅዶችን ማቋረጥ ይችላል። የባሕርይ አደጋ ግምገማና አስተዳደር መሠረታዊ ኮርስ የማኅበረሰቡን አጋሮችና ድርጅቶች የመከላከያ ጥረቶችን ለማሻሻል ከጥቃት ጋር ተያይዘው የሚመጡ ጠቋሚዎችን ያሠለጥናል ። ለተጨማሪ መረጃ፣ Protect DC ያነጋግሩ።
ደረጃ 3፥ ደህንነት ያለው ማለፊያዎ (ሴፍ ፓሰጅ) አካባቢን ማግኘት
የሴፍ ፓሴጅ ፕሮግራም ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ሲመጡ እና ሲሄዱ የተማሪ እና የትምህርት ቤት የደህንነት ጉዳዮችን ያስተናግዳል። ሁሉም የሴፍ ፓሰጅ አካባቢዎች ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ሲሄዱ ለመጠበቅ በትብብር የሚሰሩ የትምህርት ቤት አመራሮች፣ የፖሊስ መኮንኖች፣ እና/ወይም የትራንስፖርት ስፔሻሊስቶችን ያካትታሉ። Find a nearby safe passage priority area. (በአቅራቢያ ያለው የሴፍ ፓሴጅ ቅድሚያ የሚሰጥ አካባቢን ይፈልጉ።)
የአጋር የተጠቃሚ ቁሳቁሶች፥
- District of Columbia Public Schools (የኮሎምቢያ ዲስትሪክት የህዝብ ትምህርት ቤቶች)
- District of Columbia Public Charter School Board (የኮሎምቢያ ዲስትሪክት የህዝብ ቻርተር ትምህርት ቤት ቦርድ)
- SchoolSafety.gov (SchoolSafety.gov፥ የአዕምሮ ጤና ግብዓቶች)
- SchoolSafety.gov: Mental Health Resources (SchoolSafety.gov፥ ዒላማ የሚደረግ የጥቃት መከላከል)
- SchoolSafety.gov: Target Violence Prevention (SchoolSafety.gov፥ የስጋት ግምገማዎች)
- SchoolSafety.gov: Threat Assessments (SchoolSafety.gov፥ የስጋት ግምገማዎች)
- US Cybersecurity and Infrastructure Security Agency: What to do – Bomb Threat (የUS የሳይበር-ደህንነት እና መሰረት-ልማት ደህንነት ኤጀንሲ፥ ምን እንደሚደረግ – የቦምብ ማስፈራሪያ)
- US Cybersecurity and Infrastructure Security Agency: K-12 School Security Guide (የUS የሳይበር-ደህንነት እና መሰረት-ልማት ደህንነት ኤጀንሲ፥ ከመዋዕለ-ህጻናት-12ኛ ክፍል ትምህርት ቤት ደህንነት መመሪያ)